በዓለምአቀፍ ለ113ኛ እና በኢትዮጵያ ለ48ኛ ጊዜ የተከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ ዛሬ ኤምባሲያችን ጅቡቲ ከሚገኙ የሴቶች ማህበር ጋር በደማቅ ሁኔታ አክብሯል።
በክብረ-በዓሉ ላይ የተገኙት ክቡር አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ሴቶችን ማስተማር እና ማብቃት የሁሉም ሰው ኃላፊነት መሆኑን በማንሳት ማህበሩ ሴቶችን በማደራጀት፣ የህግ ከለላ እንዲያገኙ በማገዝ፣ ማህበራዊ ድጋፍ በማቅረብ እና በማስተማር የጀመራቸውን መልካም ተግባር አጠናከሮ እንዲቀጥል መልዕክት አስተላልፈዋል።
በቀጣይ ኤምባሲው ማህበሩን በማገዝ፣ መብታቸው እንዲከበር እና አቅማቸው እንዲጠናከር አብሮ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
የማህበሩ አባላትም በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ማንኛውም አካላዊ፣ ስነልቦናዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫና ለመከላከል ሁሉም ሴት ይህን ማህበር መደገፍ እና በንቃት መሳተፍ እንዳለባቸው አስተያየት ሰጥተዋል።