የኢትዮጵያ ጅቡቲ ምድር ባቡር (በቀድሞ አጠራሩ የፍራንኮ-ኢትዮጵያ ምድር ባቡር) ግንባታው የተጀመረው በ1889 ዓ.ም ሲሆን ተጠናቆ አዲስ አበባ የደረሰው ከ20 ዓመታት በኋላ በ1909 ዓ.ም ነበር፡፡
በኢኮኖሚ ዘርፍ ያላቸውን ትስስር ከፈጠሩና ካጠናከሩ የኢትዮጵያ ተቋማት መካከል የባሕርና ትራንዚት አገልግሎት ድርጅት አንዱ ነው፡፡
የአንደኛው አገር ዜጎች በሌላው አገር በጊዜያዊነትም ሆነ በቋሚነት ሲኖሩ የሚጋጥማቸውን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ባህላዊና ሥነ ልቦናዊ ፈተናዎች ለመቋቋም እና ደስተኛና የተሳካ ሕይወት ለመምራት በማሰብ የኮሚኒቲ ማህበራት ሲያደራጁ ኖረዋል፡፡
ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ዘመናዊ የኢኮኖሚ ግንኙነት ከመሰረቱበት ከ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አንስቶ የኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋም(የኢትዮጵያ መንግሥት ባንክ) በጅቡቲ ይንቀሳቀስ እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በጅቡቲ ሥራውን የጀመረው በጉዳይ ፈጻሚ ደረጃ በ1955 ዓ.ም. ሲሆን ሙሉ የባንክ አቋም የያዘው ግን በ1962/63 ዓ.ም. ነበር፡፡
ኢትዮጵያና ጅቡቲ ከሁለትዮሽ ግንኙነት ባለፈ በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ውጤታማ ትብብርና የተሳካ ወዳጅነት ያላቸው አገራት ናቸው፡፡ አገራቱ ከኢኮኖሚያዊና ከንግድ ትስስር ባሻገር በፖለቲካው ዘርፍም በአፍሪካ ኅብረት (ቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት)፣ በፒቲኤ (Preferential Trade Area for Eastern and Southern Africa)፣ ...