አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች
- ኢትዮጵያ የተወለደ ግለሰብ ኢትዮጵያዊነቱን ለማጣራት የቀበሌ መታወቂያ፣ የትምህርት ማስረጃ ወይም ተያያዥ ሰነዶች ይዞ በመምጣት ሰነድ አልባ ቅፅ መሙላት፣
- ጂቡቲ ለተወለደ ግለሰብ የቤተሰብ ማለት የእናትና አባት ወይም የአንዳቸውን ፓስፖርት ቅጅ ማቅረብ፣
- የልደት ሰርቲፊኬት ዋናውንና ቅጅ ማቅረብ፣
- መነሻ ግድግዳቸው ነጭ የሆነ ሶስት ጉርድ 3X4 ፎቶግራፍ፣
- በኤምባሲው የጣት አሻራ መስጠት፣
የፓስፖርት ዕድሳት ለማድረግ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች
- በእጅ ላይ ያለውን ፓስፖርት ዋናውንና አንድ ቅጅ ማቅረብ፣
- ከ6 ወር ወዲህ የተነሱ መነሻ ግድግዳቸው ነጭ የሆኑ ሶስት ባለ 3X4 ፎቶግራፍ፣
- 10,800 /አሥር ሺህ ስምንት መቶ የጂቡቲ ፍራንክ/ ክፍያ መፈፀም፣
የጠፋ ፓስፖርት ምትክ ለማግኘት መሟላታ የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች
- የነባሩ ፓስፖርት ቁጥር ወይም የፓስፖርት ቅጅ ማቅረብ፣
- ከጅቡቲ ፖሊስ ስለ መጥፋቱ ማስረጃ ማቅረብ፣
- 16,200 /አሥር ስድስት ሺህ ሁለት መቶ የጂቡቲ ፍራንክ/ ክፍያ መፈፀም፣
አዲስ ፓስፖርት ለማግኘት የሚያመለክቱ ሰነድ አልባ ኢትዮጵያውያን ማሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች
- ኢትዮጵያ የተወለደ ግለሰብ ኢትዮጵያዊነቱን ለማጣራት የቀበሌ መታወቂያ፣ የትምህርት ማስረጃ፣ የልደት ወረቀት፣
የመንጃ ፈቃድ ወይም ተያያዥ ሰነዶች ይዞ ወደ ኤምባሲው በመምጣት ሰነድ አልባ ቅፅ መሙላት፣ - ጂቡቲ ለተወለደ ግለሰብ የቤተሰብ ማለት የእናትና አባት ወይም የአንዳቸውን ፓስፖርት ቅጅ ማቅረብ፣ ጅቡቲ የተወለደ መሆኑን የሚያሳይ የልደት ሰርቲፊኬት ዋናውንና ቅጅ ማቅረብ፣
- መነሻ ግድግዳቸው ነጭ የሆነ ሶስት ጉርድ 3X4 ፎቶግራፍ፣
- በኤምባሲው በመገኘት አሻራ መስጠት፣