1. በያዝነው የ2016/17 ዓ.ም. የምርት ዘመን 2.3 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ወደ ኢትዮጵያ ለማጓጓዝ እና ከክረምት ወራት በፊት ለአርሶ አደሩ ለማድረስ እቅድ ተይዞ እየተሰራ ይገኛል፡፡

ይህንን የአፈር ማዳበሪያ ዝውውር ለሁሉም ክልሎች ለማድረስ የተቋቋመው ብሔራዊ የአፈር ማዳበሪያ ቴክኒካል ኮሚቴ የስራ ሂደቱን በበላይነት የሚመራ ሲሆን ጅቡቲ ያለውን የስራ ሂደት በጂቡቲ የአፈር ማዳበሪያ ኦፕሬሽን ንዑስ ኮሚቴ በኩል ይከታተላል። ይህን ንዑስ ኮሚቴ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ በሰብሳቢነት እና ሌሎች በጂቡቲ የሚገኙ ስምንት(8) አስፈጻሚ መ/ቤቶችን አካቶ በየዕለቱ በጂቡቲ ወደብ ያለው የአፈር ማዳበሪያ የስራ ሂደት ይገመግማል፡፡

በዚህም መሠረት እ.ኤ.አ. ኖቬምበር 3 ቀን 2023 ዓ.ም. የአፈር ማዳበሪያ ጭነት የማጓጓዝ ስራ በይፋ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ እስከአሁን 17 መርከቦች 939,560.6 ሜ/ቶን የአፈር ማዳበሪያ ጭነው ጂቡቲ ወደብ ደርሰዋል። ከዚህ ጭነት ውስጥ 905,525.37 ሜ/ቶን ያህል የአፈር ማዳበሪያ ከጅቡቲ ወደብ ወደ ሀገራችን ማጓጓዝ ተችሏል፣ ይህም ጅቡቲ ከደረሰው የአፈር ማዳበሪያ 96.37% እንዲሁም ከዓመታዊ እቅዱ 46.67% ማሳካት ተችሏል፡፡ ቀሪው የማጓጓዝ ስራውም ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ይህ የአፈር ማዳበሪያ ወደ አገራችን የማጓጓዝ ሂደት የተለያዩ ችግሮች ሲያጋጥመው የጂቡቲ ኦፕሬሽን ንዑስ ኮሚቴ ተሰብስቦ ተገቢውን እርምጃ በመውሰድ እና ከኮሚቴው አቅም በላይ የሆኑ ችግሮችን ለበላይ ኮሚቴ በማሳወቅ በተቻለ ፍጥነት የኦፕሬሽን ስራውን እንዲቀጥል በተገቢው መንገድ እየሰራ ይገኛል፡፡

በዚህ የስራ ሂደት ውስጥ እስከአሁን ከታዩ ዋና ችግሮች መካከል የትራንስፖርት አቅርቦት ማነስ እና ተያያዥ ችግሮች ናቸው። እነዚህ ችግሮች ለመፍታት የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን፣ በተለይም ከተሽከርካሪ እጥረት ጋር የተነሱ ችግሮችን ከሚመለከታቸው ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በክቡር አምባሳደር እና በኦፕሬሽን ኮሚቴው በኩል ተከታታይ ውይይቶችን በማካሄድ ችግሮቹ በተቻለ ፍጥነት መፍትሄ እንዲያገኙ እና የአፈር ማዳበሪያው በታቀደለት ጊዜ ወደ አገር ቤት እንዲገባ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።

Telegram: https://t.me/EthiopiaInDjibouti

Loading

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X