ክቡር አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ነዋሪነታቸው በጅቡቲ ካደረጉ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር በወቅታዊ በሆኑ አገራዊ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ ላይ በአጠቃላይ ወቅታዊ የሀገራችን ሁኔታ፣ በጅቡቲ ስለሚኖሩ ዜጎቻችን የመብት ጉዳይ፣ ስለህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር እና ሀሰተኛ መረጃን መከላከል ላይ ከእያንዳንዱ የዳያስፖራ አባል የሚጠበቀው ኃላፊነትን በተመለከተ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል።
በመድረኩ ከተሳታፊዎች ለቀረቡ ጥያቄዎች ማብራሪያ በመስጠት ሁሉም የዳያስፖራ አባላት አንድነታቸውን ለሀገራችን የሰላም ዘብ መሆን እንደሚገባ ተገልጿል።
በውይይቱ ላይ የኃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ከተለያዩ የልማት ማህበር አደረጃጀቶች የተውጣጡ የዳያስፖራ አባላት እና በጅቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተሳትፈውበታል።