በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ ክቡር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ የኢጋድ ዋና ጸሐፊ፣ ክቡር ዩሱፍ ሙሳን የጂቡቲ የንግድ ምክር ቤት ሊቀመንበር፣ ክቡር ኤልያስ ሙሳ ዳዋሌ የኢኮኖሚ እና ፋይናንስ ሚኒስትር፣ ክብር መሀመድ አህመድ  የግብርና ሚኒስትር፣ ክቡር መሀመድ አቡበከር የአከባቢ እና ልማት ሚኒስትር፣ ክቡር ኦማር አብዲ የሠራተኞች አስተዳደር ሚኒስትር እና በጅቢቲ የሚገኙ የሌሎች አገራት አምባሳደሮችና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ አባላት ተገኝተዋል።

በኤምባሲው የክምችት ክፍል ከተቀመጡ ፎቶዎች ፣ የቪዲዮዎች እና የጽሁፍ ሰነዶችን በዘመናዊ መልክ በማቅረብ የተዘጋጀው ይህ ኤግዚቢሽን በኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኤምባሲ ደረጃ የመጀመሪያው ኤግዚቢሽን ሆኗል።

ኤግዚቢሽኑ እስከ ነገ ድረስ ለጉብኝት ክፍት ሆኖ ይቆያል።

Loading

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X