የሀገራችን  የልዑካን ቡድን በጂቡቲ የገዢው ፓርቲ 45ኛ ዓመት ክብረ-በዓል ላይ እየተሳተፈ ይገኛል

በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ክቡር አደም ፋራህ የተመራው ልዑክ በጂቡቲ የገዢው ፓርቲ 45ኛ ዓመት ክብረ-በዓል ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።

በመርሃ-ግብሩም ላይ ክቡር አደም ፋራህ የአጋርነት ንግግር ያቀረቡ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ብልጽግና ፓርቲን ወክለው ለገዢው ፓርቲ እና ለጅቡቲ ህዝብ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

አክለውም ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ ረጅም ዓመት ያስቆጠረ የባህል እና የቋንቋ ትስስር ያላቸው ወንድማማች ህዝቦች ከመሆናቸው ባሻገር በኢኮኖሚያዊ እና በመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ዝርጋታ የጠበቀ ግንኙነት እንዳለቸው አንስተዋል። 

በመጨረሻም የብልጽግና ፓርቲ ለጂቡቲ ገዢው ፓርቲ ያለው አብሮነት እና ወንድማማች ለማስቀጠል ያለውን ቁርጠኛ አቋም በመግለጽ ንግግራቸውን አጠቃለዋል።

በተጨማሪም በክብረ – በዓሉ ላይ የቻይና፣ የኬንያ እና ሩዋንዳ ልዑክ ተገኝተዋል።

Loading

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X