በቀጣዮቹ ሳምንታት ከ1 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ጂቡቲ ይደርሳል

 

በመጪዎቹ ሁለት ሳምንታት 1 ሚሊየን 274 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ጂቡቲ ወደብ እንደሚደርስ የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን አመላከተ፡፡

 

ለ2016/17 የምርት ዘመን ከተገዛው የአፈር ማዳበሪያ ውስጥም 510 ሺህ ኩንታል ዩሪያ የጫነች ‘አባይ ሁለት’ መርከብ ጂቡቲ ደርሳለች።

 

እስከአሁንም 9 ሚሊየን 395 ሺህ 606 ኩንታል ማዳበሪያ ወደብ ደርሰሏል።

 

ከዚህ ውስጥም 8 ሚሊየን 731 ሺህ 403 ኩንታል ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዞ በመሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማኅበራት አማካኝነት ለአርሶ አደሮች እየቀረበ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

 

በመጪዎቹ ሁለት ሳምንታትም 834 ሺህ ኩንታል ኤን ፒ ኤስ እና 440 ሺህ ኩንታል ዩሪያ በአጠቃላይ 1 ሚሊየን 274 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ጂቡቲ ወደብ እንደሚደርስ ይጠበቃል፡፡

Loading

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X