(የካቲት 28/2016ዓ.ም) በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ማህበር የ2016 ዓ.ም የስድስት ወር የአፈጻጸም ሪፖርት ክቡር አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ የስራ አስፈፃሚ አባላት በተገኙበት አቅርቧል። 

ስራ አስፈፃሚው ያቀረበውን ሪፖርት መነሻ በማድረግ በገቢ ማሰባሰብ ስራዎች፣ አባላትን የማፍራት፣ ማህበራዊ ድጋፍ የማቅረብ፣ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የማጠናከር እና የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን መስጠት ዙሪያ ሰፊ ወይይት ተደርጓል።

 

ክብር አምባሳደር በንግግራቸው በውይይቱ ላይ የቀረቡ የማሻሻያ ሃሳቦችን በመጨመር በቀጣይ ሊሰሩ የሚገባቸውን የትኩረት አቅጣጫዎች ለይቶ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

Loading

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X