በጅቡቲ የሰላም እና ባህል ማበልፀጊያ ኢንስቲትዩት (Moderation and Culture of Peace Institute) በይፋ ተመረቀ
በጅቡቲ የሰላም ና ባህል ማበልፀጊያ ተቋም (Moderation and Culture of Peace Institute) የጅቡቲው ፕሬዝደንት ክቡር ኢስማኤል ኦማር ጊሌ፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምከር ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር ሸህ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ እና የኢፌዴሪ አምባሳደር ክቡር ብርሃኑ ፀጋዬ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ግብዣ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በይፋ ተመርቋል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸህ ሐጂ ኢብራሂም ንግግር ያደርጉ ሲሆን የኢትዮጵያ እና የጅቡቲ ህዝቦች የረዥም ጊዜ ታሪካዊ ወዳጅነት በማንሳት የመሰል ተቋማት መገንባት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን የበለጠ እንደሚያጠናከር ገልፀዋል።