(የካቲት 23 ቀን 2016 ዓ.ም.) በጅቡቲ የኢፌዲሪ ኤምባሲ በጂቡቲ ካሉ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ አባላት፣ ከሃይማኖት አባቶች እና ከተለያዩ የመንግስት ተቋማት ከተውጣጡ የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን 128ኛውን የአድዋ ድል በዓል በኤምባሲው ቅጥር ግቢ አክብሯል።

የሚሲዮኑ ምክትል መሪ ክቡር አቶ ከበደ አበራ በመክፈቻ በንግግራቸው አድዋ በዓል የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የሁሉም የጥቁር ህዝቦች ድል መሆኑን በመግለጽ ይህን ታሪክ ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍ የሁሉም ኃላፊነት መሆኑን አንስተዋል።

አክለውም በጂቡቲ ለመገንባት የታቀደውን የኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤት ግንባታ ስራ ላይ ሁሉም ዜጋ በመሳተፍ ከዳር እንዲያደርስ እና የዘመኑን አድዋ ታሪክ በመድገም ለቀጣይ ትውልድ እንዲያስተላልፍ አሳስቧል።

የአድዋን ገድል የሚያትት አጭር ማብራሪያ እና የፓናል ውይይት በኤምባሲው የመከላከያ አታሼ የቀረበ ሲሆን ታዳሚውም በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የታየው አንድነት በሌሎች ሃገራዊ ስራዎች ላይ መጠበቅ እንዳለበት ሃሳባቸውን በመስጠት የዕለቱ መርሃ-ግብሩ ተጠናቋል።

Loading

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X