ሚሲዮኑ ጅቡቲ ከሚገኘው የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ቢሮ ጋር በመተባባር በሳምንቱ ውስጥ 35 ፍልሰተኞች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ አደረገ፡፡
ከተመላሽ ፍልሰተኞች መካከል 20 ያህሉ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ሲሆን 3 በፍልሰት ወቅት የወለዱ እናቶችን ጨምሮ 7 ያህሉ በየመን በአስከፊ ችግር ውስጥ ቆይተው ወደ ጅቡቲ የገቡ ናቸው። ቀሪዎቹ ደግሞ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ለመሻገር ጅቡቲ ከገቡ በኋላ ባህር የመሻገር ሀሳባቸውን ለመቀየር የተገደዱ ናቸው፡፡
ከኢትዮጵያ- ጅቡቲ- የመን የሚደረገው ህገ-ወጥ የሰዎች ፍልሰት በሞትና ልዩ ልዩ አደጋዎች የተሞላ በመሆኑና በተለይም በዚህ ወቅት የጅቡቲ ሙቀት በከፍተኛ ሁኔታ ስለሚጨምር፣ ኤምባሲያችን የአገራችን ወጣቶች በህገ-ወጥ ደላሎች የውሸት ስብከት በመታለል ውድ ህይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው በዚህ አደገኛ የጉዞ መስመር ከመንቀሳቀስ እንዲቆጠቡ መልዕክቱን ያስተላልፋል።