ኢጋድ በቀጣናው ሰላም እና ደህንነት ለማጠናከር ለሰሩ አካላት በዛሬው ዕለት እውቅና ሰጥቷል።

እውቅና የተሰጣቸው ተቋማት ኮሚሽነሮች የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል እና የጅቡቲ ብሔራዊ ፖሊስ ዳይሬክተር ጄነራል ኮሎኔል አብዱራማን አሊ ካህን  ናቸው።

ኢጋድ የሁለቱ ሀገራት ፖሊስ ኮሚሽኖች ቀጣናዊ ትስስሩን የሚያጠናክር ስራ እየሰሩ መሆኑን ገልፆ፣ ለዚህም ተግባር እውቅና የሰጠ መሆኑን የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ገልፀዋል።

ጅቡቲ በሚገኘው የኢጋድ ዋና ጽ/ቤት በተካሄደ ስብሰባ ላይ የተገኙት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በበኩላቸው፣ በሁለቱ ሀገራት ፖሊሶች መካከል ያለውን ትስስር ለማጠናከር በ2021 የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው በጋራ የድንበር አካባቢ ጥበቃ ማጠናከር እና የፖሊስ አቅም ግንባታ ስራዎችን ለመስራት ማስቻሉን ጠቁመዋል።

አክለውም፣ የሁለቱ ሀገሮች ፖሊሶች በቅንጅት በህገወጥ የሰዎች እና የጦር መሣሪያ ዝውውር፣ በገንዘብ ነክ ወንጀሎች፣ የፀጥታ እና የሰላም ጉዳዮች በጋራ በመስራት ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በመጨረሻም፣ የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ሁለቱ ሀገራት በሰላም እና ደህንነት ዙሪያ እያከናወኑ ያሉትን ጠንካራ ስራ ለመደገፍ ቃል ገብተዋል።

Loading

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X