የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) የዋና ጸሀፊው ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁን የስራ ዘመን ለተጨማሪ አራት ዓመታት አራዘመ።
በተጨማሪም በትላንቱ የኢጋድ ስብሰባ፤ አባል ሀገራት በዙር በሚደርሳቸው የሊቀመንበርነት ኃላፊነት ስልጣን ላይም ለውጥ ተደርጓል። ላለፉት አራት ዓመታት ኢጋድን በሊቀመንበርነት ስትመራ የቆየችው ሱዳን የዛሬውን ጉባኤ ላስተናገደችው ጅቡቲ ኃላፊነቱን አስረክባለች። ኢትዮጵያ ይህን የኃላፊነት ቦታ ለሱዳን አሳልፋ ከመስጠቷ በፊት ለዘጠኝ ዓመታት ኢጋድን በሊቀመንበርነት መምራቷ ይታወሳል።
በትላንቱ የመሪዎች ጉባኤ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ጨምሮ የጅቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ኬንያ እና ደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንቶች ተሳትፈዋል። በሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ እና በሶማሊያ ጉዳዮች ላይ በዋነኛነት መክሯል።