በጅቡቲ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ በጅቡቲ ከሚገኘው የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ቢሮ ጋር በመተባባር 66 ፍልሰተኞች በባቡር ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ አደረገ፡፡   

ከፍልሰተኞች መካከል 57ቱ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ለመሻገር ጅቡቲ ከገቡ በኋላ ደላሎች ምድረበዳ ላይ ተሰውረውባቸው በIOM መጠለያ ጣቢያ የገቡ ናቸው፡፡ 9 ያህሉ ደግሞ በየመን በአስከፊ ችግር ውስጥ ቆይተው ወደ ጅቡቲ የገቡ ናቸው፡፡ 

ፍልሰተኞቹ በህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች በመካከኛው ምስራቅ አገራት በአጭር ጊዜ ለመክበር በሚል የቀቢጸ ተስፋ ምኞት ተታልለውና ከፍተኛ ገንዘብ ከፍለው ነው ከሀገራቸው የወጡት፡፡  ፍልሰተኞቹ በመሸጋገሪያና መዳረሻ ሀገራት ለረሃብ፣ ለውሃ ጥም፣ ለጤና መታወክ፣ ለከፍተኛ እንግልትና ተያያዥ ችግሮች ተዳርገዋል፡፡             

ከኢትዮጵያ- ጅቡቲ- የመን የሚደረገው ህገ-ወጥ የሰዎች ፍልሰት በሞትና ልዩ ልዩ አደጋዎች የተሞላ በመሆኑ፣ ኤምባሲው የአገራችን ወጣቶች በህገ-ወጥ ደላሎች የውሸት ስብከት በመታለል ውድ ህይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው በዚህ አደገኛ የጉዞ መስመር ከመንቀሳቀስ እንዲቆጠቡ መልዕክቱን ያስተላልፋል።

Loading

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X