በዓለም ለ112ኛ ጊዜ፤ በአገራችን ለ47ኛ ጊዜ  የተከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በጅቡቲ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የኤምባሲው ሰራተኞች በተገኙበት በድምቀት አክብሯል።

በበዓሉ ላይ ክቡር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ መሪ ክቡር አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፤ በጅቡቲ የሚገኙ ሴት የዳያስፖራ አባላት የተፈናቀሉ ዜጎችን በማገዝ፤ ቦንድ በመግዛትና በማንኛውም አገራዊ ጥሪ በግንባር ቀድምነት በመሰለፍ እስካሁን ላበረከቱ አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ችግሮችና መንስዔዎቻቸውን ለማቃለል ብሎም ለማስወገድ የሚቻለው የችግሩ ሰለባዎች የሆኑት ሴት ዜጎቻችን ንቁ ተሳትፎ ሲያደርጉ ብቻ ነው ያሉት አምባሳደሩ፣ በጅቡቲ የሚገኙ ሴቶች ተሳትፎውም በተበታተነ መንገድ ሳይሆን በተደራጀ ሁኔታ በአንድ ድምፅ አብረው ለመብታቸውና ጥቅማቸው በጋራ መሥራትና ጠንካራ ማህበር በመፍጠር ንቁ ተሳትፎ ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

በመቀጠልም በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ትምህርት ቤት ግንባታ እና ሀብት የማሰባሰብ ሂደት ላይ ሴቶች ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ጥሪ አስተላልፈዋል።

በዝግጅቱ ላይ በማህበር መደራጀት አስፈላጊነት፣ በማህበር ከተደራጁ ሴቶች የሚጠበቅ ውጤት፣  በጅቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሴቶች የተደራጁ ያለመሆን ያስከተለው ችግር እና ቀጣይ የመፍትሄ አቅጣጫዎችና መፍትሄዎቻቸውን የተመለከተ መነሻ ጽሁፍ ቀርቦ የፓናል ወይይት ተደርጓል። 

በጅቡቲ የሚገኙ የአገራችን ዜጎች ያላቸውን ማህበራዊ መስተጋብር ለማጠናከር እንዲሁም ችግሮችን ለመፍታት የሴቶች ማህበር ማጠናከር አስፈላጊነቱን ያነሱት ተሳታፊዎች፣ የዛሬ ዓመት የተመሰረተው የሴቶች ማህበር የአንድ አመት ሪፖርቱን ያቀረበ ሲሆን የአዳዲስ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴዎች ምርጫም አካሂዷል።

Loading

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X